=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
ነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) የተወለዱት የመጀመሪያው ሰው አደም(ዐ.ሰ) የመጀመሪያውን የአምልኮት ቤት የቆመባት የጥንት የሰው ልጅ መኖሪያ ከሆነችው መካ ከተማ ነው። ይህ ከተማ አረቢያ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን በአንፀባራቂ አሸዋና ገላጣ ኮረብታዎች የተሸፈነና በቀይ ባህርና በሶሪያ መካከል የሚገኝ ትልቅ የበረሃ መሬት ነው። ይሁንእንጂ በሂጃዝ ክልል ውስጥ ትንሽ ለምለም ቦታ ይገኛል።
የሙስሊሞች የስልጣኔ መፍለቂያ ፣ የአለም የከተሞች እናት የሆኑት መካ ፣ መዲና ጅዳ የሚገኙት በዚሁ ክልል ውስጥ ነው....Read more
በባሪያ ንግድ ወቅት ያች ወጣት ኢትዮዺያዊት ሴት በረካ እንዴት መካ ውስጥ ለሽያጭ እንደበቃች ባይታወቅም እንዲሁም የዘርሃረጓ፤ እናቷ ማን እንደሆነች ፣ አባቷ ማንእንደሆነ ወይም ቅድመአያቶቿ ማን እንደሆኑ ባይታወቅም እሷን መሰል ወጣት ወንዶችና ሴቶች አረቦችም ሆኑ አረብ ያልሆኑ ነገርግን ተይዘው ወደ ባሪያ ገበያ ለሽያጭ የበቁ በርካቶች ነበሩ።
በመጥፎ የባሪያ ገዥዎች እጅ የወደቀ ባሪያ መጥፎ እድል የሚገጥመው ሲሆን አብዛሃኛዎቹም ጉልበታቸውን ከልክ በላይ ይበዘብዟቸዋል ከልክ በላይ በሆነ ግፍና በደል ይይዟቸዋል። በዚህ ሁኔታ ላይ እድለኞች የሆኑ እጅግ በጣም ጥቂቶች ናቸው።
ወጣት ኢትዮዺያዊት ሴት በረካ ከእድለኞቹ መካከል ስትሆን ደግና ቸር የነበረው የአብዱል ሙጦሊብ ልጅ አብዱሏህ የራሱ አደረጋት። በእርግጥም በቤቱ ውስጥ ብቸኛዋ አገልጋይ ሆነች። አብዱሏህ አሚናን ባገባ ጊዜ በረካ(ረ.ዐ) ሁሉንም ጉዳዮቿን የምትጠብቅ እና የምትቆጣጠር....Read more
በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት አቡ ኹረይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት
ጅብሪል(ዐ.ሰ) ወደ ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) መጣና እንዲህ አለ፦ "የአሏህ መልዕክተኛ ሆይ! ለየት ያለ ምግብ እና መጠጥ ወደ አንተ ይዛ የምትመጣው ኸድጃ ናት። ወደ አንተም በደረሰች ጊዜ በአሏህ ስም ሰላምታ አቅርብላት። በጀነት ውስጥ ምንም ጫጫታም ሆነ ልፍት የሌለበት የሆነ፤ ከቀሰብ የተሰራ ቤተ-መንግስት ያላት መሆኑን የምስራች ስጣት" አለ።
ጠንካራ ባህሪዋና ታላቅ ስብዕናዋ በጅብሪል አማካኝነት የአሏህን ሰላምታ በማግኘት ይህን የመሰለ ክብር አግኝታለች። ታማኝ ፣ ሃቀኛ ፣ መልካም ባህሪን የተላበሰች ፣ ለጋስ ፣ ቸር ፣ ምራቋን የዋጠች ሴት ስትሆን ያደገችውም በሃብትና በቅንጦት ላይ ነበር።
ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ጥሪ ባደረጉላት ጊዜ እስልምናን ሃይማኖቷና የህይወት ጎዳናዋ አድርጋ የተቀበለች የመጀመሪያዋ እንስት እሷ ናት። በአሏህ(ሱ.ወ.ተ) እና በጅብሪል(ዐ.ሰ) ሰላምታ የቀረበላት ሲሆን በዚህ በኩል ክብርን ያገኘች የመጀመሪያዋ ሴት ናት።....Read More
ኢማድ አድዲን ኢስማኤል ኢብን ኡመር ኢብን ከሲር አል-በስሪ አዲመሽቂ የተወለዱት በ700 ዐ.ሂ ሲሆን አባታቸው የሞቱት የሰባት አመት ልጅ እያሉ ነው።
በታላቅ መንድማቸው በመታጀብ ወደ ደማስቆ አቀኑ፤ ብዙ እውቀት ከኢብን ሻኪር አል-አመዲ እና ከለሌሎችም ሻቱ።
ከሚታወቁባቸው ስራዎች መካከል....Read more
አንድ አይነበሲር ልጅ ከአንድ ህንፃ መወራረጃ ላይ ኮፍያ ይዞ ተቀምጧል፤ ልጁም አይነበሲርነኝ እባካችሁ እርዱኝ የሚል መልዕክት የያዘ ሲሆን ከኮፍያው ያሉት ሳንቲሞች ትንሽ ነበሩ። አንድ ሰው በጎኑ እየተጏዘ እያለ ከኪሱ ሳንቲሞችን አውጥቶ ወደ ኮፍያው አስገባለትና ልጁ የያዘውን መልዕክት አንስቶ ገለበጠና አዲስ ፅሑፍ ፅፎለት በልጁ ጐን የሚያልፉ ሰዎች እንዲያዩት ለእይታ ምቹ በሆነ መልኩ ፅፎ....Read more
ሁለት በአደን(የበረሀ እንስሳት) በመያዝ እሚተዳደሩ ሰዎች ነበሩ። ሁለቱም ለዘመናት ያህል አብረዉ ይሰሩና አበረው ይኖሩ ነበር። ነገር ግን አንደኛው ከአማኞች ሲሆን ሌላኛው ግን ከእምነት ወጪ ነበር።
ከእለታት አንድ ቀን አደን ላይ ዉለዉ አንድ ቦታ ላይ ለዕረፈት ተቀምጠው ጠመንጃቸወን(መሳርያቸዉን) እየወለወሉ(እያጸዱ) እያለ....Read more
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|